የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 13ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ
በኢ.ፌ.ድ.ሪ ንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ 366(1)፣ 367(1)፣370፣393(1) እና 400(1) እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀፅ 5 መሠረት የግሎባል ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤና 13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ጦርሀይሎች አካባቢ በሚገኘው ኡማ ሆቴል ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤ ላይ እንድትገኙልን የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
-
- የአክሲዮን ማህበሩ የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
1.1 የአክሲዮኑ ማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ፣ አራዳ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 01 ሱማሌ ተራ ግሎባል ሕንፃ ላይ ይገኛል፡፡
1.2 የማህበሩ ድህረ ገፅ WWW.globalinsurancesc.com
1.3 የንግድ ምዝገባ ቁጥር አአ/ግማ/23372/39
1.4 የመድን ሥራ ፈቃድ ቁጥር 008/97
1.5 የማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ብር 337,099,000
1.6 የማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) 329,947,500
- የአክሲዮን ማህበሩ የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
-
- የ28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1 አጀንዳ ማፅደቅ
2.2 ከ27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በኋላ የተደረጉ የማህበሩን አክሲዮን ዝውውሮች እና አዳዲስ አክሲዮን የገዙ ባለአክሲዮኖችን መቀበል
2.3 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ
- የ28ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
-
- የ13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ
3.1 አጀንዳ ማፅደቅ
3.2 የማህበሩን መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀፅ 1 እና አንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 2 ካፒታል እና አክሲዮኖችን በተመለከተ ማሻሻያ ማድረግ
3.3 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ
- የ13ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ
-
- ማሳሰቢያ
4.1 በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀፅ 377 መሠረት ጉባኤው ከማካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት በዋናው መስረያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ለዚሁ አላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካይም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡
4.2 የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሰተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማኅበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈ መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
- ማሳሰቢያ
የግሎባል ኢንሹራንስ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ
